Գլխավոր էջ Biblical Principles for Reconciliation and Good Cultural Practices

Biblical Principles for Reconciliation and Good Cultural Practices

0 / 0
Որքա՞ն է ձեզ դուր եկել այս գիրքը:
Ինչպիսի՞ն է բեռնված ֆայլի որակը:
Բեռնեք գիրքը` գնահատելու դրա որակը
Ինչպիսի՞ն է բեռնված ֆայլերի որակը:
Addis Ababa: SIL Affiliated International Ministry, 2015. - 36 p., il.የማስታረቅ አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች እና መልካም ባሕላዊ ልምምዶች. Брошюра о христианских моральных принципах и ценностях. Пагинация разнонаправленная (разворотами).
Կատեգորիաներ:
Լեզու:
amharic
Էջեր:
20
Ֆայլ:
PDF, 13.30 MB

Ձեզ կարող է հետաքրքրել Powered by Rec2Me

 
0 comments
 

To post a review, please sign in or sign up
Կարող եք ակնարկ թողնել գրքի վերաբերյալ և կիսվել ձեր փորձով: Մյուս ընթերցողներին նույնպես հետաքրքիր կլինի իմանալ ձեր կարծիքը իրենց կարդացած գրքերի վերաբերյալ: Անկախ նրանից՝ ձեզ դուր է գալիս գիրքը, թե ոչ, եթե անկեղծորեն և մանրակրկիտ պատմեք դրա մասին, մարդիկ կկարողանան իրենց համար նոր գրքեր գտնել, որոնք կհետաքրքրեն իրենց:
የማስታረቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች
መጽሐፍ ቅዱስ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ብቻ ሳይሆን በምድር ላይ
ስንኖር ከሰዎች ጋር ጤናማና መልካም ምሳሌነት ያለው የፍቅርና
የሰላም ኑሮ እንድንኖር ይመክረናል። ሰዎች ነንና አልፎ አልፎ
በመካከላችን አለመስማማትና ግጭት ቢፈጠር እንዴት ባለ ሁኔታ
እርቅና ሰላም መፍጠር እንዳለብን እንዲሁም የተጣሉትን ወገኖች
በእንዴት ያለ ጥበብ ማስታረቅ እንዳለብን መሠረታዊ መርሆዎችን
ይሰጠናል። ከእነዚህ መርሆዎች መካከል ጥቂቶቹ በዚህ አነስተኛ
መጽሐፍ ለምሳሌነት ተጠቅሰዋል።

Title: የማስታረቅ አገልግሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎች እና መልካም
ባሕላዊ ልምምዶች
Title in English: Biblical Principles for Reconciliation and Good

Cultural Practices

Language: Amharic as spoken in Ethiopia
Type of book: spiritual
Illustrations by: Senait Werku © 2015
Used with permission.
Author: SIL AIM Scripture Engagement Department
July 2015

First Edition
1,000 copies

© SIL AIM

ኤስ አይ ኤል ኤ አይ ኤም

SIL Affiliated International Ministry
Addis Ababa, Ethiopia

2. አንድ ሰው በንብረት ላይ ጉዳት ቢያደርስ
 የበደለው ሰው የተበደለውን ሰው በሽማግሌዎች አማካይነት
ይቅርታ እንዲያደርግለት ይለምናል።
 የተበደለው ሰው ከአሁን በፊት በተመሳሳይ ግጭት የጎሳው
አባላት ካሳ መቀበላቸውን ካጣራ በኋላ ካልተቀበሉ እርሱም
ካሳውን አይቀበልም፤ነገር ግን በውል ይቀመጣል። ከዚህ
በፊት ካሳ የተቀበለ ካለ ካሳውን ይመልሳል።
 በመጨረሻም ሽማግሌዎች እንዲህ አይነት ግጭት ዳግመኛ
እንዳይፈፀም ማስጠንቀቂያ ሰጥተው የእርቁ ሥነ ስርዓት
በዚሁ ይፈፀማል።
3. አንድ ሰው ቀለል ያለ ጥፋት ቢያጠፋ ወይም ቀለል ያለ ጉዳት
በንብረት ላይ ቢያደርስ፣ አጥፊው ወደተበደለው ሰው
ሽማግሌ በመላክ ብቻ እርቀ ሰላም ይሆናል ወይም ይቅርታ
ይደረግለታል።

36

የማስታረቅ አገልግሎት መጽሐፍ
ቅዱሳዊ መርሆዎች እና መልካም
ባሕላዊ ልምምዶች
Biblical Principles for Reconciliation
and
Good Cultural Practices

የማስታረቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መርሆዎች
መጽሐፍ ቅዱስ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ብቻ ሳይሆን
በምድር ላይ ስንኖር ከሰዎች ጋር ጤናማና መልካም
ምሳሌነት ያለው የፍቅርና የሰላም ኑሮ እንድንኖር
ይመክረናል። ሰዎች ነንና አልፎ አልፎ በመካከላችን
አለመስማማትና ግጭት ቢፈጠር እንዴት ባለ ሁኔታ
እርቅና ሰላም መፍጠር እንዳለብን እንዲሁም የተጣሉትን
ወገኖች በእንዴት ያለ ጥበብ ማስታረቅ እንዳለብን
መሠረታዊ መርሆዎችን ይሰጠናል። ከእነዚህ መርሆዎች
መካከል ጥቂቶቹ በዚህ አነስተኛ መጽሐፍ ለምሳሌነት
ተጠቅሰዋል።
1. የተጣሉትን ሁለቱንም ወገኖች ማወቅ ያስፈልጋል።
አስታራቂዎች የተጣሉትን ሰዎች ማንነት፣ ባሕርይ
እና ተግባራቸውን ማወቃቸው ለማስታረቅ
አገልግሎታችው ይጠቅማቸዋል።

2

35

በደራሼ ብሔረሰብ ባሕል
1. አንዲት ልጃገረድ ከተጠለፈች ሽማግሌዎች ወደ ተጠለፈችው
ልጃገረድ ዘንድ ሄደው ጠለፋው የተካሄደው በፈቃዴ ነው
እንድትል ይለምኑአታል።














የልጁ ቤተሰብ ሽማግሌ ልከው ወደ ሸንጎ እንድትቀርብ
ይደረጋል።
በሸንጎው ላይ ቀርባ ጠለፋው የተፈጸመው በራሷ ፈቃድ
መሆኑን ከገለፀች ወደ ባሏ ትሄዳለች።
አባትየውም የደረሰውን ጉዳት በመዘርዘር ካሳ ይጠይቃል።
ሽማግሌዎች ያንን ካሳ ያስፈጽማሉ።
ባሏ ወደ ልጅቱ ቤተሰብ እንደገና ሽማግሌዎችን;  ይልካል።
ድርድር ከተደረገ በኋላ ጥሎሽ ለወላጆቿ ይሰጣል።
በመጨረሻም ድግስ ተደግሶ ሁለቱም ቤተሰብ ከተገባበዙ
በኋላ እርቅ በመካከላቸው ይደረጋል።
በማስገደድ ነው ካለች ወደ አባቷ ትሄዳለች፡፡
አባትዬው ልጀቱ ያለፈቃዷ በመጠለፏ ካሳ ይጠይቃል።
ሽማግሌዎችም በማግባባት ካሳው ተቀባይነት እንዲያገኝ
ያደርጋሉ።

34

3

2. የተፈጠረውን ችግር በዝርዝር ማወቅ ያስፈልጋል።
የችግሩን ምንነት ከችግሩ ባለቤቶች መረዳት
አለባቸው።
3. ችግሩ የሚያመዝንበት ላይ (በተበዳዩ ላይ) ትኩረት
ማድረግ ያስፈልጋል።
ትኩረት ማድረግ የሚያስፈልገው የተበደለው ሰው
ለእርቁ የተዘጋጀ እንዲሆን ነው።
4. የተጎዳውን ሰው መልካም ተግባር መዘርዘር
ያስፈልጋል።
መልካም ተግባሩን መዘርዘር የሚጠቅመው አሁንም
መልካም እንዲያደርግ ለማበረታታት ነው።
5. አስታራቂው ስለራሱ ሁኔታ ጠቅሶ በትህትና፣
በፍቅር እና በልመና መቅረብ ይኖርበታል።
ስለ ራሱ ሁኔታ ሲባል ስለ አስታራቂው መልካም
ምሥክርነት ማለት ነው።

4

33





የጠላፊው ቤተሰቦች ለተጠለፈችው ልጅ ቤተሰብ ጥሎሽ
ያመጣሉ።
ከዚያም ተጋቢዎቹ የልጅቷን ቤተሰብ እግር ሊስሙ
ይመጣሉ።
የሚያቀርቡት ጥሎሽ ሙሉ ቁጥር መሆን አለበት።
በዚህ ሁኔታ እርቅ ይፈፀማል።

በ·ሌ ብሔረሰብ ባሕል










አንድ ሴት በሌላ ሰው ተደፍራ ካረገዘች ሽማግሌዎች ልዩ
ልዩ ምርመራ ያደርጋሉ።
ያስረገዛትም ሰው ለሽማግሌዎች ምርመራ ትክክለኛ መልስ
እንዲሰጥ ይጠበቅበታል።
ባልዬው ከተቀበላት የሚወለደውን ልጅም ተቀብሎ
ያሳድጋል
ብዙ ጊዜ ባልዬው ሴቲቱን ባይቀበላትም ካሳ ተቀብሎ
ከምታገባው ሰው ጋር በሰላም እንድትኖር ከሁሉም ጋር እርቅ
ያደርጋል።
ሽማግሌዎች ያስረገዛትን ሰው ለጥፋቱ የሚመጥን ቅጣት
ይጥሉበት እና ከከፈለ በኋላ ከሴትዬዋ ባል ጋር
ያስታርቁታል።
ዋናው ሽማግሌ እርጥብ ቅል ለሁለት ሰንጥቆ ከቅሉ ውስጥ
የሚገኘውን ውሃ እና ፍሬ በሴትዬዋ ላይ ይረጭባታል።
ከዚያም ከባሏ ጋር እንድትታረቅ ይደረጋል።

32

5

6. የአጥፊውን (የሌላውን ወገን) መልካም ሁኔታ
መጥቀስ ያስፈልጋል።
ተበዳዩ የአጥፊውን መልካም ተግባር
እንዲያስተውልና ለይቅርታ እንዲዘጋጅ ለማድረግ
ይጠቅማል።
7. ማስታረቅ መስዋዕትነትን ሊጠይቅ ይችላል ለዚህም
ዝግጅትን ይጠይቃል።
የጊዜ፣ የገንዘብ እና ራስን ዝቅ የማድረግ
መስዋዕትነት ሊጠይቅ ይችላል።
8. ጥልቅ ጉዳትን ፈጽሞ ይቅር ለማለት ጊዜ
ይወስዳል።
ውጫዊ ቁስል ለመዳን ጊዜ እንደሚወስድበት
ውስጣዊ ጉዳትም እንዲሁ ለመዳን ጊዜ ይወስዳል።
9. ይቅርታ በደለኛው በሚያደርገው ነገር ላይ
አይወሰንም።
በደለኛው አንድ መልካም ነገር ስላደረገ ሳይሆን
ይቅርታ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ስላመንበት
መሆን ይገባል።

6

31

በዛይሴ ብሔረሰብ ባሕል
1. በመስኖ ውሃ ምክንያት ግጭት ከተፈጠረ




በሁለቱም ወገን ሽማግሌዎች ይመረጡና የተጣሉት ወገኖች
በሽማግሌዎች አማካይነት እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲታረቁ
ይደረጋል።
ያጠፋው ሰው ለሽማግሌዎች ካሳ እንዲከፍል ይደረጋል
ቅጣቱን ሽማግሌዎች ይወስናሉ።

2. በእርሻ መሬት ድንበር ምክንያት ግጭት ከተፈጠረ






የተጎዳው ሰው ሽማግሌ ይልካል
ሽማግሌዎች ቦታውን በጋራ ይመለከታሉ
ሽማግሌዎች ድንበሩን ወስነው ያስሟሟቸዋል
ከዚያ እጅ ለእጅ ተያይዘው ይታረቃሉ
ለሽማግሌዎችም አዋጥተው ገንዘብ ይሰጣሉ።

3. የጠለፋ ጋብቻ







የጠላፊው ወንድሞች እና ቤተሰቦች ገንዘብ ይዘው ወደ
ልጅቷ አክስቶች ይሄዳሉ።
ለአክስቶች እና ለእናቶች ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት
ቁጣውን ያበርዳሉ።
ዋና ሽማግሌ የልጅቷን አባት ይመክራል ያባብላል።
ሌሎች ሽማግሌዎች በልጅቷ አባት ደጅ ላይ እየተንከባለሉ
ይለምናሉ።
ይህንን ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ ያደርጋሉ።

30

7

10.ይቅርታ በቀልን ለእግዚአብሔር መተው ነው።
የእኛ ድርሻ መፍረድ ሳይሆን ይቅርታ ማድረግ ብቻ
ነው።
11.ይቅርታ ሕመማችንን ወደ ኢየሱስ ማምጣትን
ይጨምራል።
በግጭቱ ምክንያት የደረሰብንን ጉዳት ወይም የውስጥ
ጉዳት ወደ ኢየሱስ በጸሎት ማቅረብና እርሱ
እንዲፈውሰን እንዲሁም ለይቅርታ እንዲያዘጋጀን
መጸለይ ያስፈልጋል።
12.ይቅርታ ከቁጣ እና ከቂመኝነት ነፃ ያደርገናል።
13.ይቅርታ ማድረግ የእግዚአብሔርን ይቅርታ
እንድንቀበል ይረዳናል።
‹‹ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ የሰማዩ
አባታችሁም እናንተን ይቅር ይላችኋል››
ማቴዎስ 6፡14

8

29

በኮንሶ ብሔረሰብ ባሕል



















በሰዎች መካከል ነፍስ ከጠፋ ሽማግሌዎች የሟቹን ጎሳ ዋና ሰው
ያማክራሉ።
ሶስት ጊዜ ወደ ሟች ቤተሰብ መጥተው ከተመለሱ በኋላ
በአራተኛው በሩን ያንኳኳሉ ቤተሰቡም ካስገባቸው በኋላ
ድርድሩ ይጀመራል።
የሟች ቤተሰብ በእርቁ ሂደት ከተስማማ በኋላ በገዳዩ ጎሳ መሪ
አማካኝነት ወይፈን፣ የአንድ አመት ጠቦት በግ፣ ቄብ ፍየል እና
ጊደር እንዲመጣ ያደርጋሉ።
ከዚያም ተቀበሉን ብለው የሟችን ቤተሰብ ይጠይቃሉ።
እነርሱም ይቀበላሉ።
በአመቱ መጨረሻ ላይ እንዲሁ ለሁለተኛ ጊዜ ይደረጋል።
በሦስተኛ ጊዜ ገዳዩ ከሽማግሌዎች ጋር ሆኖ ሦስት መቶ ብር
እና አንድ ቅል ማር ይዞ ይመጣል። የጎሳ መሪዎችም ይገኛሉ
ድግስም ይደረጋል።
የሟች ቤተሰብ ጫቃ የሚባለውን መጠጥ ይቀምሳል ለገዳዩም
ቤተሰብ ይሰጣሉ።
የሟች ወንድም (ታላቅ ወይም ታናሽ)ጫቃውን ይቀምሳል
ለገዳዩም ይሰጣል።
ገዳዩና የሟች ቤተሰብ ተወካዮች ይጨባበጣሉ።
ዋናው ሽማግሌ ተነስቶ ከአሁን በኋላ አንድ ሆነናል ይላል።
ሁሉም እንዲሁ ይላል። የእርቁ ስርዓትም በዚሁ ይፈፀማል።

28

9

14.ይቅርታ የክርስቶስን መስዋዕትነትንና የእኛን መዳን
መረዳታችንን ያሳያል።
እግዚአብሔር እኛን በክርስቶስ ይቅር ያለን እኛም
የበደሉንን ይቅር እንድንል ነው።
15.ይቅርታ ከበደሉን ሰዎች ጋር እርቅ እንድናደርግ
ይረዳናል።
ይቅርታ ማድረግ ከእርቅ ይቀድማል ይቅርታ
ከልባችን ካደረግን ለእርቁ ሂደት ጥሩ ሁኔታን
ይፈጥርልናል።
16.ይቅርታ የበደለንን ሰው ሊለውጥ ይችላል።
ይቅርታ ስናደርግ የበደለን ሰው በድርጊታችን ተነክቶ
የባሕርይ ለውጥ ሊያሳይ ይችላል።
17.የበደልነው እኛ ከሆንን በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ
መግባት እና የበደልነውን ሰው ይቅርታ መጠየቅ
አለብን።
18.ቤተ ክርስቲያን የተጣሉትን ሰዎች እርስ በእርሳቸው
ወደ እርቅ እንዲመጡ መርዳት ትችላለች።

10

27








እርቁ በዚያው ይፈፀማል።
ሁለቱም ወገኖች አብረው ምግብ ይበላሉ።
እርቁን ያደረጉበት በግ አይበላም።
የሟች ቤተሰብ ከገዳዩ ቤተሰብ ምንም ዓይነት ካሳ
አይቀበልም። ካሳውን መቀበል የሟቹን ደም እንደመጠጣት
ይቆጠራል።
በእለቱ ለመጡት ሰዎች ሌላ በግ ወይም ከብት ይታረድና
ተጠብሶ ይበላሉ።

26

11

የማስታረቅ አገልግሎት
መልካም ባሕላዊ ልምምዶች
በአገራችን በሁሉም ባሕሎች ውስጥ የተጣሉትን ሰዎች ጎሳዎችና
ብሔረሰቦች ለማስታረቅ የሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የታዋቂ
ግለሰቦች፣ የቤተ ሰብ መሪዎች እና የእናቶች ሚና ከፍተኛ ነው።
ስለሆነም በተወሰኑት ብሔረሰቦች ውስጥ ከሚካሄዱት የማስታረቅ
መልካም ልምምዶች መካከል የሚከተሉት ለምሳሌነት ከዚህ በታች
ተጠቅሰዋል።

ከሱሪ ብሔረሰብ ባሕል
1. አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ጉዳት አድርሶ የተጣላ ከሆነ
 ሽማግሌዎችን ጠርቶ እንዲያስታርቁት ይጠይቃል።
 ሽማግሌዎችም በጥዋት ወደተበደለው ሰው ቤት ይመጣሉ።
 ተበዳዩ ግለሰብ ቤቱን ከፍቶ ሲወጣ ሽማግሌዎችን
ይመለከታል ከዚያም ለምን እንደመጡ ይጠይቃቸዋል።
 እነርሱም ከእርሱ ጋር የተጣላው ሰው ለሽማግሌነት
እንደላካቸው ጠቅሰው ይቅር እንዲልና እንዲታረቁ
ይጠይቁታል።
 ብዙ ውይይትና ምክክር ከተደረገ በኋላ እርቁ ይፈጸማል።

12

25

3. በአንድ ብሔረሰብ ውስጥ መገዳደል ሲከሰት ፤ ብሔሩ አንድ
በመሆኑ፣ ወንዛቸውም አንድ በመሆኑ ፣ ከብቶች የሚሰማሩበት
ስፍራም አንድ በመሆኑ ግጭቱ ከፍተኛ ስጋት ያሳድራል።
ስለሆነም፡





የገዳዩ ቤተሰብ ወደ ሟች ቤተሰብ ሽማግሌ መላኩ ግድ
ነው።
ሽማግሌዎች ከእግዚአብሔር በታች ናቸው፣ የፈሰሰ ውሃም
እንደገና አይታፈስም ተብሎ ይነገራል።
የቡና ቅጠል በትንንሽ ቅሎች ከመጣ እህል ውስጥ
ይጨመራል፤ከዚያም እህሉ ይቀላቀላል በዚያም ቂሙ
ይቀራል ተብሎ ይታመናል።
ወደ ሜዳ ይወጡና ደሙ እንዴት እንደሚሰረይ ስርዓት
ያደርጋሉ። ከዚያም እርጥብ ቅል ለሁለት ይሰነጠቅና
ከሽማግሌዎች ዋና የሆነው በቅሉ ውስጥ ያለውን ውሃ እና
ፍሬ ወደ መሬቱ (ሳር)ይረጫል በዚህም በሳሩ ላይ የፈሰሰው
ደም ይታጠባል ተብሎ ይታመናል።

24

13

2. በሁለት ቤተሰብ መካከል ግጭት ተፈጥሮ የሰው ሕይወት ካለፈ
 የገዳዩ ቤተሰብ 3 ሰዎች ይቅርታ ለመፈለግ ወደ ሟች
ቤተሰብ ይሄዳሉ ነገር ግን በቀጥታ ወደ ቤታቸው
አይገቡም፤ በሩቅ ሆነው ከሟች መንደር ታዋቂና የተከበረ
ሽማግሌ አስጠርተው በሁለቱ ቤተሰብ መካከል ሆኖ የእርቁን
ሂደት እንዲያስጀምር ይለምኑታል።
 ሽማግሌው ወደ ሟች ቤተሰብ ሄዶ ይወያያል፡፡
የሚስማሙበትንም ሁኔታ ይጠይቃል ቀጠሮም ይይዛል።
 ወደ ገዳዩ ቤተሰብ መጥቶ የሟች ቤተሰብ የተስማሙበትን
እንዲያመጡ ይነግራቸዋል። በዚህም መሠረት፡ ቃጭል
 መጥረቢያ
 ጨሌ
 ጠቦት በግ እንዲያመጡ ያዛቸዋል። ቀጠሮም
ይይዛል።
 በቀጠሮው እለት በሟች ግቢ የሁለቱም ቤተሰብ በአንድ ላይ
ይሰበሰባሉ።
 ገዳዩ ጠቦት በግ ተሸክሞ ይመጣል።
 በዚህን ጊዜ የሟች ቤተሰብ ለሟቹ ያለቅሳሉ።
 ሽማግሌዎቹ የበጉን ፈርስ በገዳዩ ቤተሰብ ላይ ይረጫሉ።
 የገዳዩ ቤተሰብ ታላቅ የሆነ ሰው በቆዳ ላይ ይቀመጣል።
 የሟቹ ቤተሰብ ዋና የሆነ ሰው ተነስቶ ለሟች ቤተሰብ
አይዞአችሁ ሰው መጥቶአል በኋላ ትጠግባላችሁ ብሎ
ያጽናናቸዋል።

14

23



ደም ከተፋሰሱ ወይም ሰዎች ከሞቱ ሽማግሌዎች፡ የገዳዩ ብሔር በግ እንዲያመጣ ይጠይቃሉ
 በጉን የሚባርከው የገዳዩ ብሔረሰብ ሽማግሌ ነው
 የበጉ ቆዳ ሳይገፈፍ ሆድ እቃው ይቀደድና
የሁለቱም ብሔር ሰዎች እጃቸውን በፈርሱ
ውስጥ ያደርጋሉ
 በመጨረሻም የእህልና የቡና ግብዣ
ተደርጎ የእርቁ ሥርዓት
ይጠናቀቃል።

22





በቆዳው ላይ የተቀመጠው የገዳዩ ቤተ ሰብ ዋና ሰው
በተራው ተነስቶ አይዞአችሁ መጥቻለሁ ትጠግባላችሁ
ይላል።
ከዚያም የሟች ወንድም ታላቅ ወይም ታናሽ ይነሳል፤
እንዲሁም ገዳዩ የበጉን ዝልዝል ሥጋ ይጠብሱና በተላያየ
አቅጣጫ ሆነው እየበሉ ወደ መሃሉ ሲደርሱ ይገናኛሉ
በዚያው ይታረቃሉ። ሁሉም ሰው በአንድ ላይ ግብዣ
አድርጎ እርቁ ይፈጸማል።

15

16

21

20

17

ከፀማኮ ብሔረሰብ ባሕል
1. አንዲት ያገባች ሴት ብታመነዝር ወይም ከባሏ ውጭ ከሌላ
ወንድ ጋር ብትተኛ
 የባሏ ቤተሰብ ሽማግሌዎችን ይዘው ነገሩ እውነት መሆኑን
ከሴትየዋ ጠይቀው ያረጋግጣሉ።
 ነገሩ እውነት ከሆነ ሽማግሌዎች ያቺን ሴትና ያመነዘረውን
ሰው ከባሏ ጋር ለማስታረቅ ጥረት ያደርጋሉ። ባልየው ግን
ከእርሷም ሆነ ካመነዘረው ሰው ጋር በቀላሉ ላይታረቅ
ይችላል።
 ከባሏ ቤተሰብ ዋና የሆነው እርጥብ ቅል ለሁለት ከፍሎ
በመሬት ላይ ካስቀመጠ በኋላ በመካከሉ ሴትየዋን
ያሳልፋታል። ከዚያም ከቅሉ ውስጥ ያለውን ውሃ እና ፍሬ
ይረጭባታል። በዚህም ከመጥፎ ተግባሯ እንደነጻች
ይቆጠራል፤ ከባሏ ጋርም ያስታርቃታል፤ ወደ ቀድሞ
ሥራዋም እንድትገባ ይደረጋል፣ ለባሏና ለልጆቿ ምግብ
ታዘጋጃለች።
 ሽማግሌዎቹ ከሴትየዋ ጋር ዝሙት የሰራውንም ሰው ከባሏ
ጋር ያስታርቃሉ ቅጣቱንም ይወስናሉ። ያመነዘረውም ሰው
የሽማግሌዎችን ምክርና ቅጣት ተቀብሎ የወሰኑበትን ወዲያው
ያመጣላቸዋል።

18

2. አንድ ብሔረሰብ ከሌላው ብሔረሰብ ጋር ሲጣሉ
 ከሁለቱም ብሔረሰቦች የመጡ ታላላቅ ሽማግሌዎች፣ የጎሳ
መሪዎች፣ ግጭቱ ከተረጋጋ በኋላ የማስታረቅ አገልግሎት
ይሰጣሉ።
 ደም ካልተፋሰሱ ለሁለቱም ብሔረሰብ ምክር ሰጥተው
ይብቃ ይባልና እርቅ ይደረጋል።

19